Leviticus 21

ለካህናት የተሰጠ መመሪያ

1 እግዚአብሔር (ያህዌ) ሙሴን እንዲህ አለው፤ “ለካህናቱ ለአሮን ልጆች ንገራቸው፤ እንዲህም በላቸው፤ ‘ማንኛውም ሰው ከዘመዶቹ መካከል ስለ ሞተው ሰው ራሱን አያርክስ፤ 2ነገር ግን የቅርብ ዘመዶቹ ስለ ሆኑት እናቱ፣ አባቱ፣ ወንድ ልጁ፣ ሴት ልጁ፣ ወይም ወንድሙ፣ 3እንዲሁም ባለማግባቷ ከእርሱ ጋር ስለምትኖር እኅቱ ራሱን ሊያረክስ ይችላል። 4ከእርሱ ጋር በጋብቻ ለሚዛመዱት
ወይም እንደ መሪነቱ በሕዝቡ መካከል ራሱን አያርክስ።
ግን ራሱን አያርክስ።

5“ ‘ካህናት ዐናታቸውን አይላጩ፤ የጢማቸውን ዙሪያ አይላጩ፤ ሰውነታቸውንም አይንጩ፤ 6ለአምላካቸው (ኤሎሂም) የተቀደሱ ይሁኑ፤ የአምላካቸውንም (ኤሎሂም) ስም አያርክሱ። ለእግዚአብሔር (ያህዌ) በእሳት የሚቀርበውን መሥዋዕት የአምላካቸውን (ኤሎሂም) ምግብ ስለሚያቀርቡ ቅዱሳን ይሁኑ።

7“ ‘ካህናት በዝሙት የረከሱትንም ሆነ ከባሎቻቸው የተፋቱትን ሴቶች አያግቡ፤ ለእግዚአብሔር (ኤሎሂም) የተቀደሱ ናቸውና። 8የአምላክህን (ኤሎሂም) ምግብ የሚያቀርብ ነውና ቀድሰው፤ እኔ የምቀድሳችሁ
ወይም ቅዱስ አድርጌ የምለያችሁ እኔ እግዚአብሔር
እግዚአብሔር (ኤሎሂም) ቅዱስ ነኝና ቅዱስ ይሁንላችሁ።

9“ ‘የካህን ሴት ልጅ ዝሙት ዐዳሪ ሆና ራሷን ብታረክስ፣ አባቷን ታዋርዳለች፤ በእሳት ትቃጠል።

10“ ‘ከወንድሞቹ መካከል ተለይቶ በራሱ ላይ ዘይት የፈሰሰበትና የክህነት ልብስ እንዲለብስ የተቀባው ካህን የራስ ጠጕሩን አይንጭ፤
ወይም ጠጕሩን አይላጭ።
ወይም ልብሱን አይቅደድ።
11አስከሬን ወዳለበት ስፍራ አይግባ፤ ስለ አባቱም ሆነ ስለ እናቱ ራሱን አያርክስ፤ 12የተቀደሰበት የአምላኩ (ኤሎሂም) የቅባት ዘይት በላዩ ስለሆነ የአምላኩን (ኤሎሂም) መቅደስ ትቶ በመሄድ መቅደሱን አያርክስ፤ እኔ እግዚአብሔር (ያህዌ) ነኝ።

13“ ‘ካህኑ የሚያገባት ሴት ድንግል ትሁን። 14ባል የሞተባትን፣ የተፋታችውን ወይም በዝሙት ዐዳሪነት የረከሰችውን ሴት አያግባ፤ ነገር ግን ከወገኖቹ መካከል ድንግሊቱን ያግባ። 15በወገኖቹ መካከል ዘሩን አያርክስ። እርሱን የምቀድሰው
ወይም ቅዱስ አድርጌ የምለየው
እኔ እግዚአብሔር (ያህዌ) ነኝ።’ ”

16 እግዚአብሔር (ያህዌ) ሙሴን እንዲህ አለው፤ 17“አሮንን እንዲህ በለው፤ ‘በሚቀጥሉት ትውልዶች ከዘርህ እንከን ያለበት ማንኛውም ሰው የአምላኩን (ኤሎሂም) ምግብ ይሠዋ ዘንድ አይቅረብ። 18ዕውር ወይም ዐንካሳ፣ የፊቱ ገጽታ ወይም የሰውነቱ ቅርጽ የተበላሸ ማንኛውም የአካል ጕድለት ያለበት ሰው አይቅረብ። 19እንዲሁም እግሩ ወይም እጁ ሽባ የሆነ፣ 20ጐባጣ ወይም ድንክ፣ ማንኛውም ዐይነት የዐይን እንከን ያለበት፣ የሚያዥ ቍስል ወይም እከክ ያለበት ወይም ጃንደረባ አይቅረብ። 21ከካህኑ ከአሮን ዘር ማንኛውም ዐይነት የአካል ጕድለት ያለበት ሰው ለእግዚአብሔር (ያህዌ) በእሳት የሚቀርብ መሥዋዕት ሊያቀርብ አይምጣ፤ እንከን ያለበት ስለሆነ፣ የአምላኩን (ኤሎሂም) ምግብ ለማቅረብ አይምጣ። 22እርሱም የተቀደሰውንና እጅግ ቅዱስ የሆነውን የአምላኩን (ኤሎሂም) ምግብ ይብላ። 23ነገር ግን እንከን ያለበት ስለሆነ መቅደሴን እንዳያረክስ ወደ መጋረጃው አይቅረብ ወይም ወደ መሠዊያው አይጠጋ፤ የምቀድሳቸው
ወይም ቅዱስ አድርጌ የምለያቸው
እኔ እግዚአብሔር (ያህዌ) ነኝ።’ ”

24ሙሴም ይህን ለአሮን፣ ለልጆቹና ለእስራኤላውያን ሁሉ ነገራቸው።

Copyright information for AmhNASV